ነሐሴ 29/2017 በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኢንስፔክሽን እና ስነምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት የ2017በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2018 እቅድ ውይይት በማድረግ በ2017 ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ እና የጎላ አስተዋጽኦ ለነበራቸው ተቋማት እውቅና ሽልማት ሰጥቷል። በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አምደ አያሌለው እንደተናገሩት ኮሚሽኑ ከተቋቋ ዓላማ አንጻር ተገቢውን ተልዕኮ መወጣቱን ገልጸው በተለይም የፓርቲውን ውስጣዊ ጥንካሬና ህዝባዊ ቅቡልነት ማጎልበትን ላይ በትኩረት እየሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑ ተናግሯል። ቀጣይም በበለጠ ተቋም እንዲጠናከር በትኩረት መስራት እንደሚገባ አቶ አምዴ አሳስበዋል። ጠንካራ ፓርቲ በመፍጠር ጠንካራ መንግስት እንዲመሰረት የኮሚሽኑ አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ነው ያሉት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኢንስፔክሽን እና ስነምግባር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሙሉጌታ ተስፋዬ ንቁ አባላትን በማፍራትና ዴሞክራሲያዊ አስራሮች እንዲጎለብቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሆነ ገልጸዋል። በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኢንስፔክሽን እና ስነምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘህሩ አብዱሰላም በበኩላቸው ኮሚሽኑ በ2017 በርካታ ተግባራትን ማከናወን መቻሉን ተናግረው በፓርቲው ውስጥ ብልሹ አሰራሮች እንዲወገዱና በፓርቲው ውስጥ ዴሞክራሲያዊ እሳቤዎች እንዲጎለብቱ በትኩረት መስራት መቻሉን ገልጸዋል። የፓርቲው አሰራርና መመሪያ ተጠብቆ እንዲተገበር የኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን ከፍተኛ ሚና እየተወጣ መሆኑ አቶ አቶ ዛህሩ አስገንዝበዋል። የፓርቲው ጠንካራ ጎኖች እንዲጎለብቱና ጉድለቶች ተቋማዊ በሆነ መልኩ እንዲቀረፉ የተደራጀ እንቅስቃሴ መደረጉን የጠቀሱት አቶ ዘህሩ ጠንካራ የፓርቲ ተቋም ለመዘርጋት የማይተካ ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ አብራርተዋል። ቀጣይ በ2018 ኮሚሽኑ የፓርቲውን የአሰራር ስርዓትና የፖለቲካ ጤንነት ለማስጠበቅ እና በበጀት አመት ዉስጥ ጠንካራ የሆነ ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ ዉጤታማ ሥራዎችን በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል። #kirkos_prosperity
Comments:
No comments yet. Be the first to comment!